ታሪካችን

ዓለምጸሐይ ሺፈራው የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የቦሌ ክፍለ ከተማ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙት አሥራ አንድ ክፍለ ከተሞች አንዱ ነው። ክፍለ ከተማው የአዲስ አበባችን ዓለም አቀፋዊ በር፣ የኢትዮጵያ ኩራት የሆነው ብሔራዊ አየር መንገዳችንን ጨምሮ የበርካታ ታላላቅ ተቋማት መቀመጫ፣ ኤምባሲዎች፣ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ድርጅቶች የሚገኙበት፣ የከተማችን የዘመናዊነት ማሳያ እና ኅብራዊነት ደምቆ የሚታይበት ነው። 6,371 ሄክታር የቆዳ ስፋት ያለው የቦሌ ክፍለ ከተማ በአሥራ አንድ ወረዳዎች የተዋቀረ ሲሆን፣ የነዋሪው ሕዝብ ብዛት 308,995 ነው። የክፍለ ከተማችን አስተዳደር ለነዋሪው ኅብረተሰብ የሚሰጠውን አገልግሎት በማሻሻልና በማዘመን የሕዝብን እርካታ ለማሳደግ በየደረጃው በትጋት እየሠራ ሲሆን፣ በክፍለ ከተማችን በምታገኙት አገልግሎት እርካታችሁን ከፍ ለማድረግ በርትተን የምንሠራ መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ።

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለኅብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ቀልጣፋ፣ ዘመናዊ እና ችግር ፈቺ በሆነ መንገድ ለማከናወንና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በክፍተኛ ደረጃ እየሠራ ይገኛል። አስተዳደራችን ከመደበኛ ሥራው ጎን ለጎን ሰው ተኮር ተግባራትን በማከናወን በልዩ ልዩ መስኮች ተጠቃሚነትና ውጤታማነት የተረጋገጠበት ክፍለ ከተማ ለመሆን እያደረገ ባለው ጥረት የሚታዩና ተጨባጭ የሆኑ ስኬቶችን አስመዝግቧል።

ዕለታዊ ድር ጣቢያ ጎብኝዎች

ወርሃዊ የድር ጣቢያ ጎብኝዎች

አጠቃላይ የድር ጣቢያ ጎብኝዎች

ተወዳዳሪ የሌለው አገልግሎት የላቀ ልምድ
ለምርጥ መፍትሄዎች የአስተዳደር ቢሮአችንን ይጎብኙ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ምን አዲስ ነገር አለ

የቅርብ ጊዜ ዜና ልጥፎች

መጋቢት 19/2016
የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የከተማ ልማት

የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ዘርፍ ኮሚቴ በክፍለ ከተማው ተገንብተው ለአቅመ ደካማ ወገኖች የተላለፉ የመኖሪያ ሕንፃዎችን ጎበኘ።

መጋቢት 19/2016
የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን ማስፋፋት የክፍለ ከተማችን ስኬት ነው::

ስፖርት ለአካላዊ ብቃትና ለጤናማ ኅብረተሰብ መፈጠር ያለው ሚና በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በመሆኑም ለስፖርት መስፋፋት ትኩረት መስጠት አስፈላጊ ነው።